የ41 አመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል የአጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ሮቨን ቫን ፐርሲ በኤርዲቪዝዬው እየተጫወተ የሚገኘው ኸረንቪን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ግን አሁን የልጅነት ክለቡ ፌይኖርድ ቋሚ አሰልጣኝ እያፈላለጉ ነው የሚገኙት ከዛ አንፃር እግር ኳስ የጀመረበትን ክለብ እሱም በአሰልጣኝነት ለመረከብ ዝግጁ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ፌይኖርዶች የአርን ሽሎት ተተኪ ሆኖ ቡድኑን የተረከበውን ብሪያን ፕሪስኬን እንዳሰናበቱት ይታወቃል። በዚህ አሰልጣኝ ስር ኤቲሀድ ላይ ከኋላ ተነስተው ባስቆጠሯቸው 2 ጎሎች 3 አቻ የተጠናቀቀው የሻምፒዮንስ ሊግ መርሀ ግብር የሚታወስ ነው።
ቫን ፐርሲ ከሂረንቪን ጋር የሚያቆየው ኮንትራት የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሆነ ይታወቃል። ያንን ተከትሎ ፌይኖርዶች ለሊጉ ተፎካካሪዎቻቸው የካሳ ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
እንደ Espn ዘገባ ከሆነ ይህ ዝውውር እውን ሆኗል ሲል ይዞት የወጣው መረጃ ያመላክታል። በ2018 ነው ቫን ዘማን ጫማውን የሰቀለው ከዛም ከልጅነት ክለቡ አካዳሚ እና ሁለተኛ ቡድን ጋር በአሰልጣኝነት ቆይታ አድርጓል። በ2024 ግንቦት ጀምሮ ሂረንቪንን በአሰልጣኝነት ተረክቦ ይገኛል። ቡድኑን በኤርዲቪዝዬው 9ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡ አስችሏቸዋል።
ቫን ፐርሲ በጊዜው እና በሰአቱ አለማችን ላይ አስደናቂ ከሆኑ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር። ለሀገሩ ኔዘርላንድስ በ102 ጨዋታዎች 50 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
ፌይኖርዶች በሻምፒዮንስ ሊጉ ሮሳኔሪዎቹን ኤሲ ሚላኖችን አሰናብተዝ በ50 አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሎ ማለፍ ውስጥ መግባት መቻላቸው አይዘነጋም ፤ በቀጣይ ጉዞአቸውን በቋሚ አሰልጣኝ ስር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በማመን ነው ቫን ፐርሲ በአፋጣኝ ለመሾም መቃረባቸው የተሰማው።
የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚ ወይ ፌይኖርድ ወን ደግሞ PSv ናቸው። እና ፌይኖርድ ከአርርናል ጋር የሚገናኙ ከሆነ ቫንፐርሲ ቀጣዩ የፌይኖርድ አሰልጣኝ ተደርጎ መሾሙ ስለማይቀር ወደ ኤምሬትስ ለመመለስ ይገደዳል በፍፁም እዛ ስቴዲየም ላይ ጥሩ አቀባበል ከማይገጥማቸው የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋቾች መካከል አንዱ ቫን ፐርሲ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በእግርኳስ ቤተሰቡ አጓጊ አድርጎታል።
ቫን ፐርሲ እግርኳስን በፌንኖርድ ጀምሮ በፌይኖርድ ነው ያጠናቀቀው በመሀል ግን ከ2004-12 በአርርናል እንዲሁም ከ2012 አንስቶ 2015 በማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ከ2015-18 ደግሞ በቱረሰኩ ክለብ ፌነርባቼ ካሳለፈ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፌይኖርድ ተመልሶ 1 አመት ቆይታ ካደረገ በኋላ በይፋ ጫማ መስቀሉ የሚታወስ ነው።
ምላሽ ይስጡ