በኢፌዴሪ አየር ኃይል ውስጥ የተሰራችው ፀሃይ – 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወን መቻሏን አየር ኃይሉ አስታውቋል፡፡
ፀሃይ -2 አውሮፕላን ለበረራ ማሰልጠኛ እና ለሌሎች አገልግሎት መዋል የምትችል መሆኑን አየር ሃይሉ፤ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችላትን የዘመኑን የአቭዬሽን ቴክኖሎጂ ታጥቃለች ነው የተባለው፡፡
የአውሮፕላኗ ስኬታማ የሙከራ በረራ አየር ኃይሉ የደረሰበትን የከፍታ ጉዞ እንደሚጠቁም የተመላከተ ሲሆን፤በቀጣይነትም ወደ ምርት ሂደት ለመሸጋገር ፋብሪካውን የማደራጀት ፣የመፈተሻ እቃዎችን የማሟላት እና የሙያተኞችን አቅም የማጎልበት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የትራንስፖርት አውሮፕላን ስኳድሮን አዛዥ እና አብራሪ እንዲሁም የፀሃይ -2 የሙከራ በረራን በስኬት ያካሄዱት ሻለቃ ፍቃዱ ደምሴ በበኩላቸው አውሮፕላኗ አለም የደረሰበትን የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የታጠቀች የበረራ አቅሟም አስተማማኝ እና ተቋሙ ለያዘው የወደፊት ራዕይ ጉልህ አስተዋፅዖ የምታበረክት መሆኗን መግለጻቸውን የአየር ሃይሉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምላሽ ይስጡ