የቶራሲክ ሶሳይቲ የሙያ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ራሄል አርጋው በሰጡት መግለጫ የጤና ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻልና ልንከላከላቸው በምንችላቸው በሽታዎች የሚከሰቱ ህመምና ሞትን ለመቀነስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ከሙያ ማህበር ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ አብራርተዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ የሙያ ማህበር ጋር በመተባበር የአየር ንብረት ለውጥ በመተንፈሻ አካላት ጤና ላይ ያለውን ተጽዕኖ እንዴት መቀነስ ይቻላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ 11 ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
ጉባኤው The Warming World A catalyst for Respiratory Health Burdens’ በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ በመተንፈሻ አካላት ላይ እያስከተለ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑ በዚሁ መድረክ ተገልጿል፡፡
ማህበሩ ትኩረቱን በመተንፈሻ አካላትና በአየር ብክለት ላይ በማድረግ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ለጤና ሚኒስቴር ብሎም ለህብረተሰቡ መፍትሄ አመላካች ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ፕሬዘዳንቷ ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የህክምና ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ እና ብክለት ዙሪያ የጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ አሁን ላይ ሃገራችን ያለችበትን የብክለት ደረጃ በመግለጽ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምላሽ ይስጡ