ማድሪድ ከሜዳቸው ውጪ በስታዲዮ ኤል ሳዳር ከኦሳሱና ጋር 1 አቻ በተለያዩበት ጨዋታ እንግሊዛዊው ድንቅ አማካኝ ጁድ ቤሊንጋም ጨዋታውን ሲመራ ለነበረው አልቢትር ሆዜ ልዊስ ሙኒዬራን ከአፉ በወጣ አፀያፊ ቃል ወይም ስድብ ሰድቦኛል በሚል በቀጥታ ቀይ ካርድ 39ኛው ደቂቃ ላይ ከሜዳ እንዳሰናበቱት የሚታወስ ነው። አስቀድሞ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲም ቢጫ ካርድ መመልከቱ አይዘነጋም።
ተጫዋቹ ስድብ የሚባል ነገር ከአፌ አልወጣም ምናልባት እሱ የተረዳበት መንገድ ሊሆን ይችላል ሲል ሀሳብ ሰጥቷል። የስፔን እግርኳስ አወዳዳሪው አካል ጉዳዩን እየተመለከተ እንደሚገኝ መግለፁ አይዘነጋም። ታዲያ አሁን ቤሊንጋም በሁለት የላሊጋ ጨዋታዎች ላይ እንዳይሰለፍ የጨዋታ ቅጣት ተላልፎበታል።
ስለዚህ ማድሪድ በላሊጊው በሜዳቸው ከሂሮና እንዲሁም ከሜዳቸው ውጪ በቤኒቶ ቪላማሪን መነቃቃት ላይ ከሚገኘው ሪያል ቤቲስ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ማድሪዶች የቤሊንጋምን ግልጋሎት የማያገኙ ይሆናል። ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለቤሊንጋም ቀይ ካርዱን የመዘዘው አልቢትር ሆዜ ልዊስ ሙኒዬራም ጉዳይ እየተመረመረ እንደሚገኝ እና ከእግርኳስ ክለቦች ጋር ንክኪ እንዳለው ከተረጋገጠ እስከ 5 አመት ከእግርኳስ ሊታገድ እንደሚችል የስፔን ሌሊጋ እግርኳስ አወዳዳሪው አካል አሳውቋል።
ምላሽ ይስጡ