የሩሲያ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ቫለቲና ማትቬንኮ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ለአፈ-ጉባዔዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት ያደረጉ ሲሆን፤ ቫለቲና ማትቬንኮ በኢትዮጵያ ባካሄዱት የሥራ ጉብኝት በእጅጉ መደሰታቸውንና የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጠንካራና የማይናጋ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለተደረገላቸው መስተንግዶ እና አቀባበል ምስጋና ማቅረባቸውንም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምላሽ ይስጡ