ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ሞቢል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በእንጨትና በብረታ ብረት ዉጤቶች ማምረቻና በሌሎች ድርጅቶች ላይ ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የደንብ ማስከበርና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብና ቅንጅት እሳቱን በመቆጣጠር በአቅራቢያዉ ወዳሉ ሌሎች ማምረቻና ተቋማት ተዛምቶ የከፋ ዉድመት ሳያስከትል እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉ ተመላክቷል።
የእሳት አደጋዉን መንስዔ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።
በማምረቻና በንግድ ስፍራዎች አካባቢ በጥንቃቄ ጉድለትና ቸልተኝነት ምክንያት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ለጥንቃቄ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።
ምላሽ ይስጡ