የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ 100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በማስገባት በቀን 1,408 (97.5%) አውቶብሶችን በማሰማራት አገልግሎት እየሰጠ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ጂፒኤስ የተገጠመላቸውን አውቶብሶች ቁጥር ወደ 994 (95%) ማድረስ ችለናል ሲሉም ገልጸዋል።
እንዲሁም ባለፈው በጀት ዓመት የአንድ አውቶቡስ በቀን በአማካይ 8 ምልልስ ወደ 12 እንዲያድግ በማድረግ አገልግሎቱ እያሻሻልን እንገኛለን ሲሉ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ገልጸዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ