የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በየአመቱ የህብረቱ መቀጫ በሆነችው አዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
በዚህም 55 አባል ሃገራት ያሉት ህብረቱ በየአመቱ በመገናኘት የተለያዩ አህጉሩን የተመለከቱ ውሳኔዎችን ያስተላልፋሉ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች የህብረቱ አባል ቢሆኑም በጉባየው የማይሳተፉ ሃገራት እንዳሉም ይገለጻል፡፡ የፖለቲካ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኢያሱ ሃይለ ሚካኤል በህብረቱ ጉባኤ ላይ ሃገራት የማይሳተፉት የአፍሪካ ህብረት ያወጣዉን መመሪያና ህግጋት ጥሰው ሲገኙ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ውስጥ ከተሳትፎ ራሳቸውን እንደሚያገሉ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ሃገርም ሆነ የአፍሪካ ህብረት እነዚህን ሃገራት ማስገደድ እንደማትችል አንስተው ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
የቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ሃገራቱ በህብረቱ የመሳተፍም ሆነ ያለመሳተፍ መብት እንዳላቸዉ ይገልጻሉ፡፡ አንዳንድ ሃገራት የአፍሪካ ህብረቱን ማጠናከር በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን ማጠናከር ነው ብለው ስለሚያስቡ ተሳታፊ መሆን አይፈልጉም ብለዋል፡፡
ሃገራቱን ዲፕሎማሲያዊ እና አሳታፊነት በተከተለ መልኩ ማነጋገር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ አብዛኞቹ ሃገራት ለህብረቱ የሚከፈለዉን መዋጮ ሳይከፍሉ ብዙ እዳ ያለባቸዉም እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የህብረቱን ጥንካሬ ከሚፈልጉ እንደ ናይጀሪያ፣ አልጄሪያ ካሉ ሃገራት ጋር በቅርበት መስራት እንዳለባት አመላክተዋል፡፡
38ኛዉ የህብረቱ ጉባኤ የካቲት 8 እና 9 በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ