አፍሪካ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ሃብቶች የታደለች ምቹ መልካ ምድርና ከፍተኛ ቀጥር ያለው ትኩስ የሰው ኃይል ቢኖራትም በሠላም እጦት ምክንያት አፍሪካ ሃብቷን አውጥታ መጠቀም ዛሬም እንደተሳናት ቀጥላለች።
ምንም እንኳ አንዳንድ ችግሮች መነሻቸው ቀኝ ገዢዎች ትተውት ያሉፉት ችግሮች ቢሆኑም የአህጉሩ መሪዎች አስተውሎ ቶሎ መፍትሄ መስጠት ባለመቻላቸው የተነሳ አፍሪካ ዛሬም በበርካታ ዋይታ ውስጥ ትገኛለች።
በርካቶች ዛሬም በእርስ በእርስ ግጭት ፣ በመፈንቅለ መንግስትና በደህነት ሰቆቃ ውስጥ ናቸው። በዚህም የተነሳ አህጉሩ በተለይም የወጣቶች ደም እንደዋዛ የሚፈስበት፤ ወጣቶች ከልማት ይልቅ ለግጭት በስፋት የሚውሉበት በርካታ ወጣቶቿም በዚህ ምክንያት የሚሰደዱባት ከሆነች ሰነባብታለች።
ይህንኑ ጉዳይ በስፋት ተመልክተነዋል
ደጀኔ እሸቱ 👉
ምላሽ ይስጡ