የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሃገር አቀፍ ደረጃ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ የሆኑ አደጋዎች ሲከሰቱ በራሱ አቅምም ሆነ ከውጭ በሚያገኛቸው ድጋፎች ተጎጅዎችን የሚደግፍ ቢሆንም አሁን ላይ ከውጭ የእርዳታ ድርጅቶች የሚገኘው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
የውጭ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በተለያዩ ምክንያቶች የሚያደርጓቸው ድጋፎች ቀሰ በቀስ የመቀነስ እንዲሁም የማቋረጥ አዝማሚያ እንዳለ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ የእርዳታ ድርጅቶች ለድጋፉ መቀዛቀዝ እንደ ምክንያት ያነሱት በአለም ላይ ያለው የፖለቲካ ስርዓት እና በየሃገራቱ መካከል የሚደረጉ ጦርነቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የውጪ ድርጅቶች እርዳታ ሊቋረጥም ሊቀጥልም የሚችል ነገር እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ በራስ አቅም ሰበአዊ እርዳታዎችን ለመሸፈን የእርስ በእርስ መደጋገፍን በክልል በዞን እንደ ሃገርም በማጠንከር በውጭ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ላይ ጥገኛ ከመሆን መላቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡
እንደ ሃገር ያለንን የመደጋገፍ ባህል በሰፊው ማጎልበት ይገባናል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ይህን ለማድረግ ደግሞ ምርታማነትን እንደ ሃገር ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ