አዲስ አበባ በጥር ወር መጨረሻና በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የአፍሪካ ህብረት ታላላቅ ግቦች እና የፓን አፍሪካ አጀንዳዎች ጋር የተጣጣሙ ወሳኝ ተግባራትን አስተናግዳለች፡፡
ከእነዚህ ጉልህ ክንውኖች መካከል በጥር 26 ቀን 2017 በሸራተን አዲስ የተደረገዉ የፓን አፍሪካ ፕሮግራም ይጠቀሳል።የፔስቴ ዴስ ፔቲትስ ሩሚናንት (PPR) እና ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ትንንሽ አደገኛ በሽታዎችን (SRDs) ለማጥፋት የተካሄደው ለእንስሳት ጤና እድገት አንክሮ የሰጠዉ ንቅናቄ ጅምር ዋናዉ ነው።
በጎች እና ፍየሎች ላይ አስከፊ ጉዳት የሚያደርሰው የቫይረስ በሽታ እስከ 40 በመቶ የሚደርሱ የአፍሪካን በጎች እና ፍየሎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰባቸው ተገልጿል።
የፓን አፍሪካን የፔስቴ ዴስ ፔቲትስ ሩሚናንት (PPR) በ2030 ከአህጉሪቱ የማጥፋት ፕሮግራም 526 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈልገዉ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ለቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ 8 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል።
አፍሪካ ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጉ በጎች እና ፍየሎች መኖሪያ ስትሆን ከአለም አቀፉ አነስተኛ የከብት እርባታ 24% በጎች እና 31% ፍየሎች የሚሆነውን ይይዛል።
የእንስሳት ጤና ችግር አርብቶ አደር ማህበረሰቦችን ለችግር ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋሉ በተለይም በአብዛኛዉ የአህጉሪቱ ክፍል ሴቶች እና ወጣቶች በእነዚህ እንስሳት ላይ የገቢ ጥገኛ ናቸው፡፡
የሁኔታውን አስከፊነትም በመገንዘብ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) ከአፍሪካ ህብረት ዓለም አቀፍ የእንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ፣ ከየአፍሪካ ህብረት የፓን አፍሪካ የእንስሳት ህክምና ክትባት ማዕከል (AU-PANVAC)፣ ከምግብ እና የግብርና ድርጅት (FAO) እና ከዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት (WOAH) ጋር በመሆን በፒ.ፒ.አር በሽታን ክትባትን ለማስተዋወቅና በሽታዉን ከአህጉሪቱ ለማጥፋት የሚያስችል መርሃ ግብር አስጀምሯል።
ከ55ቱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት 47ቱ በበሽታዉ ተጠቂ ሆነዉ እየተሰቃዩ ነው፣ይህም አፋጣኝ የክትባት እና የቁጥጥር ስልቶችን እንዲነድፉ ገፊ ምክንያት ሆኗል።
አፍሪካ በዓመት ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው አስደንጋጭ የኢኮኖሚ ኪሳራ በበሽታዉ ምክንያት እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ይህንን ለመቅረፍና አቅም የሌላቸው ማህበረሰቦች እንዲበለጽጉ ለማድረግ አልፎም ለአህጉሪቱ የወደፊት የጠንካራ የግብርና ጤና ስትራቴጂ ሲባል ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚሰራ የአፍሪካ ህብረት ዓለም አቀፍ የእንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ዳይሬክተር ዶ/ር ሁያም ሳሊህ ገልጸዋል።
ምላሽ ይስጡ