ፈረንሳይኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ አረበኛ ፣ አፋረኛና ሱማለኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ባለፉት ሃያ አመታትም በእነዚህ ቋንቋዎች የዲፕሎማሲ ስራውን አሳልጠዋል ።
መሀሙድ የሱፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እ.አ.አ በ 1990 ከእንግሊዝ ሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት በመቀጠልም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማኔጅመንት እ.አ.አ በ1998 ከካናዳ ላቫል ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
አንድ ብለው የዲፕሎማሲ ስራውን የጀመሩት በ1990 በጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የአርብ ሀገራት ጉዳይ ዲፓርትመንት ውስጥ ነው ።
ከ1997 እስከ 2001 በግብጽ የጅቡቲ አምባሳደር በመሆንም አገልግለዋል።
ከ2001 እስከ 2005 ማለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተደርገው እስከ ተሾሙበት እለት በዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት በሚኒስቴር ማዕርግ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
በትላንትናው እለት በተካሄድወና ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነርነት ምርጫ የኬኒያውን ተወካይ ራይላ ኦዲንጋን በስድስተኛው ዙር በማሸነፍ ተምርጠዋል።
መሀሙድ የሱፍም ህብረቱ ከተመሰረተ በኋላ 7ተኛው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሁነዋል።
መሀሙድ አሸናፊ ለመሆን የሚያስፈልገውን ድምፅ ያገኙ ሲሆን ይሄም ከ49 የህብረቱ አባል ሀገራት ድምፅ፤ 33 ድምፅ በማግኘት ለቀጣይ አራት አመታት ህብረቱን በኮሚሽነርነት ይመራሉ።
በውድድሩ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ የመጀመሪያ ሁለት ዙሮችን ቢሞክሩም በስተመጨረሻ ድል አልቀናቸውም።
ኬኒያ ህብረቱን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ ያቀረበቻቸው እጩዎች ለሁለተኛ ጊዜ ሳያሸንፉ ቀርተዋል።
በ2016ም እንዲሁ ኬኒያን በመወከል የተወዳደሩት አሚና መሀመድ በሙሳ ፋኪ መሃመት መሸነፋቸው ይታወሳል።
ምላሽ ይስጡ