የአንጎላው ፕሬዝዳንት #ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ ለአንድ አመት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተደርገው ትላንት ተመርጠዋል።
* አንጎላ በአፍሪካ ሰፊ የፖርቹጋለኛ ቋንቋ ከሚነገርባቸው መካከል አንዷ ናት።
* በህብረቱ ሊቀመንበር የሚሆነው ሰው የህብረቱ ወካይ ከመሆን ባለፈ ያን ያህል የጎላ ሚና የለውም ፣
*ሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ውክልናቸውን እንዲያረጋግጡ በዙር የሊቀ መንበርነት ኃላፊነትን ይረከባሉ ፣
*ምርጫው የሚካሄደው በህብረቱ ጉባኤ ወቅት ሲሆን ፣ የአምስቱም የአፍሪካ ግዛቶች ማለትም ምስራቅ ፣ ምዕራብ ፣ ደቡብ ፣ ማዕከላዊና ሰሜን አፍሪካ ፍትሕዊ ተሳትፎ በአረጋገጠ መልኩ ይካሄዳል።
*የሊቀ-መንበርነት ሥልጣን ለአንድ አመት ብቻ ይቆያል ፣
የአፍሪካ ህብረትን በሊቀ መንበርነት የሚመራ መሪ ኃላፊነት
– ህብረቱ የሚያዘጋጃቸውን ውይይቶች ይመራል ያስተባብራል ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ ገባኤዎች ላይ ህብረቱን በመወከል ይሳተፋል ለአብነትም G7 ፣ ቻይና አፍሪካ ጉባኤ ፣ የቶክዮ ዓለም አቀፍ ጉባኤና የመሳሰሉት፣
* በአህጉሩ ያሉ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የአስታራቂነት ሚናን በመያዝ ያስተባብራል ያግዛል።
ምላሽ ይስጡ