በአፍሪካ ያለው የትምህርት ደረጃ 21ኛውን ክፍለዘመን የሚመጥን አይደለም ሲሉ በ38ኛው የመሪዎች ጉባኤ ትይዩ መድረክ ላይ ገልጸዋል። ትምህርት በአፍሪካ ከሚጠበቀው በታች ነው ያሉት በዩኒሴፍ የትምህርትና ልማት አለምአቀፍ ዳይሬክተር ሮበርት ጀንኪስ ናቸው።
በትምህርት ላይ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ከአህጉሪቱ አስቸኳይ ፍላጎት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ስለ 21ኛው ክፍለ ዘመን የትምህርት ጥራትና ደረጃ እያወራን የምንገኘው ግን በ19ኛው ክፍለዘመን የትምህርት መሰረተ ልማት ነው ሲሉ በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ተጓዳኝ ትምህርት ተኮር ጉባኤ ላይ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በመሆኑም አህጉሪቱ ጠንካራ የትምህርት ኢንቨስትመንትና ከቃል ያለፈ ቁርጠኝነት ያሻታል ሲሉ ዳይሬክተሩ በአጽንኦት የገለጹ ሲሆን ዩኒሴፍ የለውጡ አካል ለመሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ