38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ የሚጀመር ሲሆን ጉባኤው “የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን“ በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይካሄዳል።
ጉባዔው በዛሬውና በነገው ውሎው የካቲት 05 እና 06 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው 46ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ወቅት በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችንም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ምላሽ ይስጡ