በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተጠይቋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮምሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት በህብረቱ የመክፈቻ ንግግራቸው በአህጉሪቱ ያሉት የጸጥታ ችግሮች በሰላማዊ መልኩ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
በሱዳኑ ጦርነት ምክንያት ከአለም ከፍተኛውን ቁጥር ያያዙ ዜጎች ተፈናቅለው በችግር ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጸዋል።
በተመሣሣይ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሊቢያ እንዲሁም በሰሃል ቀጣና ሰፊ የጸጥታ ችግር መኖሩን ጠቅሰዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ሠላም እና ጸጥታ ላይ በሚሰራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ሁለት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
በጉባኤው እየተሳተፉ ያሉት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ