በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የሰባት ዓመት ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው በእስራት መቀጣቱን የቃሉ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በእስራት ሊቀጣ የቻለው ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሉ ወረዳ 029 ቀበሌ ልዩ ቦታው ገረገራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ ከድር ይመር መሀመድ የ 7 ዓመት ህፃን ልጅ አስገድዶ በመድፈሩ የወረዳው ፖሊስ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካደረገ በኋላ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በቴክኒክና በታክቲክ ማስረጃ ካጠናቀረ በኋላ መዝገቡን ለሚመከተው የፍትህ አካል ልኳል።
የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍረድ ቤትም ጉዳዩን ሲመረምር ከቆየ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የካቲት 04 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና ለ4 ዓመት ያህል ከማንኛውም ህዝባዊ መብቶች እንዲታገድ ተወስኖበታል ሲል የቃሉ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ