የካቲት 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል አቀባበል አድርገውላቸዋል።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ የካቲት 08 እና 09 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ