38ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በመጪዉ ቅዳሜና እሁድ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
ህብረቱ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አጀንዳዎችን በማንሳት በጉባዔው ካሉ የህብረቱ መሪዎችን የማወያየት ስራ እንደሚሰራም ይገለጻል፡፡
ይሁን እንጂ ህብረቱ በዘንድሮ ዓመት ከሚያነሷቸው አጀንዳዎች ባለፈ አማርኛን ቋንቋን የህብረቱ አንዱ አካል መሆን እንዲችል ግፊቶች አስፈላጊ ስለመሆናቸው መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አስታውቀዋል ፡፡
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት አማርኛን ቋንቋ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲደረግ በማድረግ ውስጥ ጥረቶች ስታደርግ እንደነበረም አስታዉሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ጊዜያት ወደ ተግባር መግባት እንዲችል የሚደረጉ ግፊቶች እንዲሁም ጥረቶችን እንደምትቀጥል አስታዉቀዋል፡፡
የኒው ሆራይዘን ፎር ፓን አፍሪካኒዝም ስራ አስፈፃሚ ህይወት አዳነ አማርኛን የህብረቱ የስራ ቋንቋ ማድረግ እንዲቻል አጋዥ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም አስፈላጊ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡
በቀዳሚነት በህብረቱ ከሚነገሩ ቋንቋዎች ባልተናነሰ መልኩ አቅም እንዳለው ማሳየት እንዲቻል እና በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቶን ማካተት አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል።ነገር ግን ቋንቋው የህብረቱ አንዱ አካል መሆን እንዳይችል እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን እንዳሉ አንስተው በቀዳሚነትም በየአመቱ የአፍሪካ ሀገራት እየገጠሟቸው ያለው አጀንዳ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ እንደሆነ አስረድተዋል።
አሁን ላይ 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ እየተካሄደ ሲሆን በመጪዎቹ ቅዳሜና እሁድ 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ አባላት የተለያዩ አህጉራዊ አጀንዳዎችን ይዘዉ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ