የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ የሺዳኛ በላይሁን የእብድ ዉሻ በሽታ የተገኘባቸዉ ን የማስወገዱ ስራ በተቋሙ በኩል ተጠናክሮ መቀጠሉን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ላይ የተለያዩ እንግዶች ሲመጡ አልያም አለም አቀፍ ስብሰባዎች ሲኖሩ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ ተቋም ባለቤት የሌላቸውን ውሾች ክትባት የመስጠትና እብድ ውሻ ተብለው የተለዩትን ወሾች የማስወገድ መደበኛ ስራ በተደራጀ እና በተጠናከረ መልኩ እየሰራ ይኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የእብድ ውሻ በሽታ መድሃኒት የሌለውና በቀላሉ ሊድን የማይችል ከመሆኑ አንጻር ብሎም አሁን ላይ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በኮሪደሩ ልማት ምክንያት ከሚኖርበት ቤቱ ወደሌላ ቦታ እየተዘዋወረ በመሆኑ ባለቤት የሌላቸው ውሾች እየተበራከቱ መሆናቸውን ተከትሎ ሰዎችን እንዳይተናኮሉ በማሰብ የክትትልና የመሰብሰብ ስራዎችን በመስራት የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በከፍተኛ ጥንቃቄ የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ቡድን መሪው ባለቤት እያላቸው በየ መንገዱ የሚዘዋወሩ ውሾችም ቢሆኑ ከታመሙ ውሾች ጋር ሲገናኙ የመያዝ እድላቸው ሰፊ በመሆኑ የመከላከል ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነዉ ያሉት፡፡ ውሻ ያላቸው አሳዳጊዎችም ቢሆኑ በማስከተብና እንክብካቤ በማድረግ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የማስወገድ ስራውን በተመለከተ ራሱን የቻለ ጥንቃቄ እና አወጋገድ ያለውና ለህብረተሰቡም ሆነ ለአከባቢው ደህነነት ሲባል እንደተቋም በትኩረት የሚሰራ መሆኑን በመግለጽ ፤ ባለቤት የሌላቸውን ውሾች በመለየትና የመዋለድ ና የመባዛት ደረጃቸውን መቀነስ የሚያስቸሉ ሰፊ ስራዎች ሂደት ላይ መሆናቸዉን አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ