ባለፉት ቀናት በመዲናዋ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የነዳጅ እጥረት በማጋጠሙ ረጃጅም ሰልፎች በየማደያዎች ተስተዉሏል።
ይህንን መነሻ በማድረግ መናኸሪያ ሬድዮ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮን ምክንያቱን ጠይቆል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሰጠው ምላሽ ከዛሬ ጀምሮ በቂ የነዳጅ አቅርቦት በመዲናዋ ባሉ 125 የነዳጅ ማደያዎች እንደሚኖር አረጋግጧል።
በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ እጥረቱ የተከሰተበት በጸጥታ ምክንያት የመንገድ መዘጋት በማጋጠሙ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
እጥረት ያለባቸው ማደያዎችን በተመለከተም የመለየት ስራዎች ተሰርተዉ መጠናቀቃቸዉን ፤የነዳጅ ጥያቄ አቅርበዉ ያልቀረበላቸውን እና ሙሉ በሙሉ ነዳጅ የሌላቸውን ማደያዎች ከመጠባበቂያ የነዳጅ ክምችት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
እነዚህን አማራጮች በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ከሰሞኑ የታየዉ የነዳጅ እጥረት አንደሚፈታ በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ጥበቡ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አርጋግጠዋል፡፡
አሽከርካሪዎች አሁንም ወደ ነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች የሚያመሩት በቢሮው ድህረ-ገፅ የተጋሩ መረጃዎችን ሳይመለከቱ በመሆኑ ለእንግልት እየተጋለጡ መሆኑን በመግለፅ የተስተዋሉትን ረጃጅም ሰልፎች ለመቅረፍ በየቀኑ የሚወጡ መረጃዎችን ከንግድ ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ በመመልከት አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ጠቁመዋል።
ምላሽ ይስጡ