46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በስብሰባው ላይ የአፍሪካ የወደፊት እጣ ፋንታ በጋራ ፈቃደኝነት እና ተግባር ላይ የተመሰረተ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መጭውን ጊዜ በስኬት ለመወጣት ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ አፍሪካ ችግሮችን በመቋቋም ዕድገቷን ማፋጠን እንድትችልም ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት 2063 አጀንዳን ለማሳካት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ስብሰባው ለመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችና ሌሎች ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ