ከአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ትላንት የካቲት 4/2017 ዓ.ም መቀሌ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ለሉዕካን ቡድኑ በክልሉ በኩል ጥሪ እንዳልተደረገላቸው የሚናገሩት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ጣዕመ አረዶም፤ በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ለተለያዩ አካት የሰላም ጥሪና ቅስቀሳ ሲያደርጉ እደነበር አስታውቀዋል፡፡
ከጊዜ በኋላ በክልሉ ሰላም ይሰፍናል ተብሎ ቢጠበቅም ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እየተባባሱ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ጣዕመ፤ ስጋቱ በክልሉ እጅግ አስጊ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሉ ላለው ችግር መንስኤው የህወሃት ቡድን መከፋፈል እንደሆነ የገለጹት አመራሩ፤ ልዑካኑ ትላንት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት ያደረገ ቢሆን በእነ-ዶክተር ደብረፂሆን የሚመራውንም የህወሃት ቡድን እንደሚያወያይ አስታውቀዋል፡፡
የፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ አለመፈፀሙን ተከትሎ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና በተለያዩ ግለሰቦች ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ያለውን ግጭት እና አለመግባባት በሃገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓት ለመፍታት በተደጋጋሚ ቢሞከርም ሊሳካ እዳልቻለ የተናገሩት አቶ ጣዕመ፤ ችግሩን ለመቅረፍ የተቋቋመው ካውንስል በተቀናቃኝ ቡድነች እየተፈነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ካውንሰሉ በህግ አግባብ ለመቅረፍ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያስታወቁት፡፡
በክልሉ ስለተገኙት የውጭ የልዑካን ቡድኖች በተጨባጭ ባይረጋገጥም ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስት እውቅና እንዳለው እንደሚገምት ነው አቶ ጣዕመ የተናገሩት፡፡
ምላሽ ይስጡ