የካቲት 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ቅዳሜ እና እሁድ መደረጉ ይታወቃል፡፡በምክር ቤት ዉሎም በክልሉ ያሉ የተለያዩ ችግሮች የተነሱ ሲሆን በዋናነት ማህበረሰቡን እያማረሩ ካሉ ጉዳዮች መካከል ያለ ደረሰኝ በግብር ስም የሚሰበሰቡ ክፍያዎች እና በሚሊሻዎች የሚወሰዱ ህገ -ወጥ እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ያሉ ህገ-ወጥ ኬላዎችና በክልሉ ያለ ደረሰኝ ግብር ለሚሰበስቡ ሰዎች ነዋሪዉ ግብር መክፍል እንደሌለበትና የክልሉ መንግስት እንደዚህ የሚያደረጉ ሰዎች ላይም ማጣራቶች በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመለስ አብዲሳ ለጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡
ከምክር ቤቱ አባላት አሁን ላይ ከኬላዎቹ ባለፈ በከፍተኛ ሁኔታ ሚሊሻዎች ተመጣጣኝ ያልሆኑ ርምጃዎችን በመውሰድ ህዝቡን በማማመር ላይ ይገኛሉ መንግስት ጉዳዩን አይቶ የማስተካኪያ ርምጃዎችን ይወስድ እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች የተለያዩ ክፍያዎች ያለ ደረሰኝ ህዝቡ በግድዳጅ እንዲከፍል እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ለርዕሰ መስተዳድሩ ጥያቄዎችን አቅረበዋል፡፡
ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሠጡት – የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ – ሽመለስ አብዲሳ በበኩላቸው በክልሉ አሁን ላይ ሰፋፊ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን በማመላከት ልማቱ እውን እንዲሆን ጠንካራ የግብር አሰባሰብ ሰርዓት መኖር እንዳለበትና ያ ሲባል ግን ያለ ደረሰኝ የሚሰበሰብ ግብር ካለ ማህበረሰቡ መክፍል እንደሌለበት አፅኖት ሰጥተዋል፡፡ ‹በክልሉ ያለ ደረሰኝ ግብር የሚሰበስብ ሰው ካለ እርሱ የህዝቡ ጠላት ነው ብለዋል›፡፡
በክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ችግሮች መኖራቸውን በማመን የማስተካኪያ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡ በተለይም በክልሉ ከሚሊሻዎች ጋር ለተነሳ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ – ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አሁን ላይ ማጣራቶች ተደረገው የእርምት እርምጃ እየተዋሰደ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ጨፌ ኦሮሚያ በካሄደው 8ተኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ፤ቀጣይ አቅጣጫዎችንም በማመላክት ተጠናቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ