የአይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተሯ ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ዳሬክተሯ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አስተዳደርን ለማጠናከርና የታክስ ስርዓቶችን ለማሻሻል እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን በመግለፅ የተቋማቸው ድጋፍ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡
የሀላፊዋ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረግ እና በኢኮኖሚው ላይ አዎንታዊ ሀሳቦችን መስጠታቸው ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እና ስራም ሆነ ብድር እንዲሰጡ እድል እንደሚፈጥር የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በኸረተስፋ ተናግረዋል፡፡
አይኤምኤፍ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በመሆኑ አሁን ካለው በተሻለ መልኩ ለሀገሪቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
የአይኤም ኤፍ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ የተገኘውን ለውጥና ችግሮች መመልከታቸው በዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል ያሉት ደግሞ ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ መሀመድ ኢሳ ናቸው፡፡ ሀገሪቱም ከተቋሙ የምታገኝውን ጥቅም በማሰብ አሁን ካለው በበለጠ ተሳትፎዋን ማሳደግ እንደሚገባትም አክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከአይኤም ኤፍ ከምታገኝው ድጋፍ በተጨማሪ ከሌሎችም ተቋማት ድጋፍ እና አመኔታ እንድታገኝ ሰላም ላይ መስራት እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ