🔰በመጪው የጀርመን ምርጫ የቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ ፓርቲዎች ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርካታ ተንታኞች ግምታቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
ለዚህም በርካታ የሀገሪቱ ወጣቶች እንደ ኤ.ኤፍ.ዲ ያሉ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ ፓርቲዎችን እየደገፉ እና በርካቶች ልባቸው ወደ አክራሪ ብሔርተኞች እያዘነበለ በመሆኑ ነዉ ተብሏል።
እንደ ፈረንሳይ፣ ኦስትሪያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ስፔንና ጣሊያን ባሉ የአዉሮፓ ሀገራትም፣ የቀኝ አክራሪ ብሄርተኛ ፓርቲዎች፣ ባለፉት ቅርብ ዓመታትና ወራት፣ ሀገራዊ ምርጫዎችን ከማሸነፍ ጀምሮ፣ የተሻለ ውጤት እያዝመዘገቡ ሲሆን፣ በሚሊዮን በሚጠሩ ዜጎች ዘንድ ተቀባይነትን እያገኙ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ምንም እንኳን የሽብር ጥቃት የሚፈጽሙ ጥቂቶች ቢኖሩም ይህ ሁኔታ ወደ አህጉሪቱ በመግባት ሕይወታቸውን መቀየር ለሚሹ በርካታ ስደተኞች በተለይም ለአፍሪካዊያን ከቀን ወደ ቀን ደጃፉን አጥብቆ የሚዘጋ እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡
ለዛሬው የዓለምአቀፍ ትንታኔ ዘገባችን የመረጥነው ርዕሰ ጉዳይ ነው።
የትንታኔ ዘገባውን ለማዳመጥ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
ዘላለም ዳዊት
ምላሽ ይስጡ