ተከሳሽ በፍቃዱ ተሰማ በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን በጎደሬ ወረዳ ካቦ ቀበሌ ውስጥ በቀን 22/4/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ አቶ አብነው ተሰፋዬ የተባለውን ግለሰብ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ከእኔ በራፍ ምን ልታደርግ መጣህ በሚል ሰበብ በያዘው ህገወጥ ሽጉጥ ተኩሶ በመምታት በቀኝ ታፋው ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ 2ኛ ተበዳይ የሆኑት አቶ መብራቱ ናደውን በያዘው ህገ ወጥ መሣሪያ ቀኝ እጃቸው ላይ ጉዳት በማድረስ በያዘው መሣሪያ በአካባቢ ማህበረሰብ ላይ በመተኮስ አካባቢውን ለቆ መሰወሩ ነው የተገለጸው፡፡
በድጋሜ በቀን 20/8/2016 ዓ / ም ከንጋቱ 10 ከአት ተኩል በሚሆንበት ጊዜ በዚሁ በጎደሬ ወረዳ ካቦ ቀበሌ ልዩ ቦታው የኪበኮ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ህገ -ወጥ የጦር መሣሪያውን በመያዝ በወ/ሮ ሁሌም ገሊቶ የመኖሪያ ቤት በመሄድ ተነሱ በፍቃዱ ነኝ በማለት በር በማንኳኳት በሩ ሳይከፈትለት ሲቀር እርሳቸው ባለመኖራቸው ሌላ በቤት ውስጥ ያሉት ሟች ወ/ሮ እድገት ከድር የተባሉት የ6ቀን ነፍሰጡር እናትን በቤቱ ቀዳዳ በኩል በመተኮስ ሟች ወ/ሮ እድገት ከድር ህፃኗን ጡት እያጠቡ ተኩሶ በቀኝ በኩል ጡቷ ላይ በመምታት ገድሏል።
ሌላ ሟች አስራት ተስፋዬን ጭንቅላቱን በቀኝ ጆሮው በታች በመምታት የገደለ ሲሆን ተከሣሹ ወንጀሉን ከፈፀመው በኋላ ከአካባቢው ተሰውሮ የአከባቢውን ህብረተሰብ ሲበጠብጥ ከቆየ በኋላ በተደረገው የፌደራል ፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሎ ተካሳሽ በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል እና ከባድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል እንደተከሰሰ የክሱ መዝገብ ያብራራል።
የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ1997 ዓ/ም ተሻሽሎ የወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539(1)(ሀ) እና አንቀጽ 555 (ሀ) እና (ሐ) ስር የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ የቀረበ የወንጀል ክስ መሆኑን አስረድቷል።
በመሆኑም ተከሳሽ አቶ አባይነህ ተሾመ በፈፀመው ከባድ የግድያ ወንጀል እና ከባድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱና በመረጋገጡ የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የካቲት 4/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ጎደሬ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ