ከዛሬው ተጠባቂ የሻምፒዮንስ ሊግ የknock out Play-off ጨዋታዎች በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጠው የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የትኛው ማንቸስተር ሲቲ በዚ ጨዋታ ላይ እንደሚቀርብ እንደማያውቅ እና ያለንን አቅም የሚያሳየው ጠንካራውን ሲቲን ንቀርባል ብዬ እገምታለሁ ካለ በኋላ Sacked in the morning ወይም ነገ ከስራህ ትሰናበታለህ የሚለውን ጉዳይ በብዙም እንደማያሳስበው እና ስንብትን እንደማይፈራ ተናግሯል።
ስኬታናው እና አንጋፋው አሰልጣኝ ፔፕ ጊርዲዮላ ባሳለፍነው ህዳር ወር አዲስ የ2 አመት ውል መፈረሙ አይዘነጋም። ዶክተር ፤ አርክቴክት ፤ እና አስተማሪዎች እንደኛ ስራቸውን እንዲለቁ አይጠየቁም እኔ ግን የምሄድበት ስቴዲየም ሁሉ ነገ ትሰናበታለህ ይሉኛል ምኞታቸው ቢሳካ እኔም ደስ ይለኝ ነበር ግን አይመስለኝም በፊት ባሳካሁዋቸው ነገሮች ምክንያት ዝም ተብያለሁ አለበለዚህ ግልፆ እኮ ነው እሰናበት ነበር ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል። ሲቲ በ23 ጨዋታዎች 11ዱን በሽንፈት ነው ያጠናቀቁት። በክለቦች ትልቁ የውድድር መድረክ በሆነው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ምዕራፍ 22ኛ ደሰጃን ይዘው በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፍ ውስጥ ለመግባት ዛሬ ምሽት የአውሮፓውን ሀያል ክለብ እና የዚህ የውድድር ምዕራፍ የአምና ሻምፒዮኖቹን ሪያል ማድሪድን የሚጋብዙበት የኤቲሀዱ ጨዋታ ይጠበቃል።
በአሰልጣኝነት የ3 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማድሪድ በምንም ሁኔታ እና አቋም ማድሪድ ነው አምና ሜዳችን ላይ የሰጡንን ከባድ ጊዜ የሚታወስ ነው። ስለዚህ ቀላል ፈተና አይደለም የሚጠብቀን ፤ ለዛሬው ጨዋታ ምን አይነት ተነሳሽነት ያለው ማንቸስተር ሲቲ ወደ ሜዳ ይገባል የሚለውን ማወቅ አልችልም እኔም እንደ እናንተ ስቴዲየም ውስጥ ነው የማየው ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንህ ተርፒን ይመራዋል ምሽት 5:00 ሲል የሚከናወን ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በሳምንቱ በሳንቲያጎ ቤርናቦ የሚከናወን ይሆናል።
በሚካኤል ደጀኔ
ምላሽ ይስጡ