የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሕንድ 5ኛ የመንገደኛ በረራ መዳረሻ ወደምትሆነው ሀይድራባድ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ከሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀይድራባድ ከተማ በሣምንት ሦስት ቀን የሚደረግ አዲስ በረራ እንደሚጀምር ገልጿል፡፡
የዚህ በረራ መጀመር አየር መንገዱ በሕንድ የሚኖረውን የበረራ አድማስ ከማስፋቱም በተጨማሪ በአፍሪካ እና እስያ መካከል ያለውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ከፍ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
ምላሽ ይስጡ