በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሽ አቶ እሳቱ ዳንጎረ የተባለው የ60 ዓመት አዛውንት ጽኑ እስራት የተወሰነበት ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ የግል ተበዳይ የ9 ዓመት ህጻን በጎች እየጠበቀች ባለችበት ሸንኮራ እንቺ በማለት አታሏዋት ወደራሱ አቅርቦ አስገድዶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድፍረት ወንጀል በመፈፀሙ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ ግለሰቡ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ አቤቱታ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል የሰውና ሀኪም ማስረጃ በማሠባሠብ ምርመራዉን አጣርቶ ለዐቃቤ ህግ አቅርቧል።
አቃቤ ህግም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ ለወረዳው ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል።
ክሱን ሲመለከት የቆየው የወረዳዉ ፍርድ ቤት አከራክሮ ጥር 27 ቀን2017 ዓ.ም በዋለው 1ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ እሳቱ ዳንጎሮ በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ ጽፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ