በ2025 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ስራ እስካሁን 6 የዩሪያ እና የዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ ደርሰው ጭነታቸውን በማራገፍ የአፈር ማዳበሪያውን ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የማጓጓዝ ስራ መሰራቱን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
ሌሎች 7ተኛ እና 8ተኛ መርከቦች በሂደት ላይ እንደሚገኙ አስታውቆ፤በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ 5 መርከቦች ጂቡቲ ወደብ ይደርሳሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም በአጠቃላይ በ2025 በጀት ዓመት ከተያዘው ዕቅድ ውስጥ 13 አፈር ማዳበሪ የጫኑ መርከቦች ከጂቡቲ ወደብ የሚስተናገዱ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ