አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው ሁሉም ምርቶች ብሔራዊ የደረጃ ምልክት መጠቀም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅትና ለብሌስ አግሮ ፉድ ኢንዱስትሪ ውክልና በመስጠት ብሔራዊ የደረጃ ምልክት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል ።
አሁን ላይ ግን ኢንስቲትዩቱ ውክልናውን በማንሳት ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ አስገዳጅ ደረጃ ለወጣላቸው ምርቶች ብሄራዊ የደረጃ ምልክት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በሀገሪቱ ለ370 ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ መውጣቱን ጠቁመው እነዚህ ምርቶች ብሄራዊ የደረጃ ምልክት ካልተጠቀሙ ርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተናግረዋል ሲል ፋሚኮ ዘገቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ