በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የጤና መድህን አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር መገለጹ ይታወቃል።
የተቋረጠውን አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይሁን እንጅ በክልሉ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት፤ የበጀት እና የሰው ኃይል እጥረት ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑን ነው በኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የመቀሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀረጋዊ በላይ የተናገሩት፡፡
በክልሉ በአዲስ መልክ የጤና መድህን አገልግሎት ለማስጀመር መመሪያ እና የክፍያ ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም 206 ሰራተኞች እንዲቀጠሩ የማድረግ እንዲሁም ማህበረሰቡ አሁን ባለበት የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የአገልግሎቱን ክፍያ መፈጸም ስለማይችል 50 በመቶ የሚሆነውን በተቋሙ መሸፈን እንዲያስችል የሃብት ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ በዚህ ሒደት በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙ እንዳሉ ነው ስራ አስኪያጁ ያስታወቁት።
የምዝገባ ሂደቱን በታህሳስ ወር ለማስጀመር የታቀደ ቢሆንም በታቀደው የጊዜ ቀጠሮ ማስኬድ ባለመቻሉ አሁን ላይ ከወረዳና ቀበሌዎች መረጃ በማሰባሰብ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት አመት በክልሉ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደ ቢሆንም በርካታ ተግዳሮት ስለመኖሩ ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ