ጥር 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉ የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት እንደተፈረደባቸው ተሰምቷል።
ሌላ ሀገርን በመርዳት 16 ክሶች የቀረቡባቸው ሜንዴዝ፣ ቢያንስ 15 ዓመታት ሊያስፈርድባቸው ይገባ እንደነበር ተመላክቷል።
በተለይ ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት በማሰረጃነት ቀርቧል ነው የተባለው።
በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጫና አድርገው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
ምላሽ ይስጡ