ጥር 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
የረቂቁን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ ረቂቅ አዋጁ ትምህርትን በእኩልነት እና ፍትሃዊነት በመላ ሀገሪቷ ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
እንዲሁም ረቂቅ አዋጁ የመምህራንን ጥራት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የትምህርት አስተዳደሩን ብቃት ለማረጋገጥ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም፣ የአስተማሪነት ሙያ እንዲከበር እና በሂደትም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሰብሳቢው ገልጸዋል።
ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1368/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞ፣ በአሥር ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
ምላሽ ይስጡ