በኢትዮጵያ አየር መንገድ አካል ጉዳተኞችን ለመብት ጥሰት የሚዳርጉ በርካታ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች እንዲስተካከሉ ማስደረጉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ለደንበኞች በሚሰጣቸው አገልግሎቶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረጉ እና መብታቸውን የሚጋፉ በርካታ ሂደቶች እንደነበሩ የተናገሩት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች ህጻናት አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረ ሐዋሪያ፣ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል እና የአየር መንገዱ እንዲያስተካክላቸው በሰጠው ምክረ ሃሳብ በርካታ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንደተቀረፉ ገለጸዋል፡፡
የፍተሻ ቦታዎች ምቹ አለመሆንን ጨምሮ፣ ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ የሚሰጥ የባለሙያ እጥረት እና ሌሎች በአየር መንገዱ ባለው የአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ፣ በተለይ በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርሱ በርካታ የመብት ጥሰቶች እንዲታረሙ መደረጉን ነው ያመላከቱት፡፡
ለአብነትም ለአይነ ስወራን ምቹ እና ተደራሽ ያልነበረው የአየር መንገዱ ኦንላይን የትኬት መቁረጫ መተግበሪያ፣ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል እና በሰጠው አስተያየት መስተካከሉን ጠቅሰው፣ የዊልቸር እና ሌሎች ተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መሻሻላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኮምሽኑ ባደረገው ክትትል ከተስተካከሉ ክፍተቶች ባሸገር ወደ ፊት መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች ለማስተካከልም አየር መንገዱ የጊዜ ሰለዳ መያዙን በይፋ እንዳስታወቃቸው የሚናገሩት ኮሚሸነሯ ከአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መስማማታቸውንም አመላክተዋል፡፡
መሰል የአገልግሎት ተደራሽነት ችግር ያሉባቸው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ እና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ አሰራሮችን እንዲዘረጉ ኮሚሽኑ ክትትል እንደሚያደርግም ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ