ጥር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ያለንበት የጥር ወር በርካታ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ኹነቶች የሚደረግበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም መካከል በደብረ ታቦር ከተማ በጉጉት ከሚጠበቁ ኹነቶች ውስጥ አንዱ የፈረስ ጉግስ ይገኝበታል፡፡
በመሆኑም ስርዓቱን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ጥናታዊ ጹሁፎች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ያስታወቀው የደብረ-ታቦር ከተማ አስተዳደር ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ-ጉባዔ አቶ በላይ ሃይለማርያም እንደሚሉት በከተማዋ ከታህሳስ ወር ጀምሮ እስከ ጥር ወር መጨረሻ የሚከበሩ እና ተከብረው ያለፉ በዓላት መኖራቸውን ገልጸው፤በቀጣዮቹ ጊዜያትም ከሚጠበቁ በዓላት መካከል አንዱ የቅዱስ መርቆሪዮስ የንግስ በዓል እና የፈረስ ጉግስ እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡
በዚህ በሚካደው ኹነት ላይ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ፈረሰኞች ጥሪ እንደተላለፈላቸዉና ፤ለበዓሉ ድምቀት ትልቁን አስተዋጽዖ ያበረክታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል፡፡
አክለውም ከተማዋ ከፍተኛ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን እንዲሁም ጥንታዊ ቅርሶችን አቅፋ የያዘች በመሆኑ ማስተዋወቅ እንዲቻል በማድረግ ውስጥ ስርዓቱ አጋጣሚዎችን ይፈጥራልም ብለዋል፡፡
አያይዘውም በዓሉ በየዓመቱ የሚጠበቅ ስርዓት ከመሆኑ ባለፈ የገቢ ምንጭ እንዲሆን እና ኢትዮጵያም ተጨማሪ ሃብቶችን ማግኘት እንድትችል በማድረግ ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ማስመዝገብ አስፈላጊ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥናት እንዲሁም የምርምር ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ምክትል አፈ-ጉባዔው አመላክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባህላዊ ትውፊቶቿን ማሳየት የምትችልባቸው በርካታ ኹነቶች እንዳሏት ይታወቃል፡፡ በርካታ ሃብቶችን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም ፤ሌሎች በርካታ ሃብት መሆን የሚችሉ ሁነቶች እንዳሏት የሚታወቅ ነዉ፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ