ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጋብቻዉ ቁጥር በዘለለ የሚሰማ የፍቺ ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ መንግስት ለጋብቻ እና ቤተሰብ መጽናት የሚሆኑ ፓሊሲና የተለያዩ ህጎችን በማዉጣት ከለላ ማድረግና ጋብቻ እና የቤተሰብን ጉዳይ የሚከታተል ቢሮ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ ሊያቋቋም እንደሚገባ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸዉ የጋብቻ አማካሪዎች ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ቤተሰብ ለጤናማ ሀገር ዋስትና እና መሰረት በመሆኑ እየታዩ ያሉ ጤናማ ያልሆኑ ትዳሮች አስቀድሞ መከላከል እንዲቻል ስለ ጋብቻ፤ ስለ ቤተሰብ፤ ስለልጆች አስተዳደግ እና ሌሎችም ቤተሰባዊ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶባቸዉ በህግ እና ስረዓት እንዲመሩ ማድረግ ይገባል ያሉት የጋብቻ አማካሪዉ አቶ ይመስገን ሞላ ናቸዉ፡፡
ቤሰተብን የሚጠብቅ ፓሊሲ ቢዘጋጅ ትዳር በቀላሉ እንዳይፈርስ እና አለመግባባቶች በመነጋገር እንዲፈቱ ትልቅ ሚና የማጫወት ዕድል እንደሚኖረዉም አስረድተዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብ እና ስነ ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃዲ መንግስት የህግ ከለላ ለማስቀመጥ ጥናት ስለሚፈልግ በቀጣይ የሚሰራበት ነዉ በማለት ገልጸዉ በቀዳሚነት ግን ሰዎች ከመጋባታቸዉ በፊት ዝግጁነታቸዉን ራሳቸዉን ቢፈትሹና ማረጋገጥ ቢችሉ የፍች ቁጥርን ለመቀነስ አጋዥ እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡
ቤተሰብ የሃገር መሰረት በመሆኑ መንግስት የሃይማኖት አባቶች ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ይህን ትልቅ ተቋም በመጠበቅ ዉስጥ ያለበትን ሃላፊነት እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ