ጥር 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በገና በዓል የተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በተለይም የምርት መደበቅ ሁኔታ እንዳይፈጠር ከንግድ ቢሮ ጋር እንዲሁም ማህበረሰቡን የሚያውኩ ተግባራት እንዳይፈፀሙ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እንዲሁም ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመጣመር ከፍተኛ ቁጥጥር መደረጉን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሰረት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ሁኔታዎች የደንብ ጥሰት በፈፀሙ 280 የሚሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልፀዋል፡፡
በገና በዓል ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን በመለየት በቀጣይ ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጀምሮ በአመራሮች ደረጃም በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት በጋራ እንደሚሰራ እና በግልፅም ሆነ በስውር የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ጥረት እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በዓላትን ተከትሎ የምርት መደበቅ፣የህገ-ወጥ እርድ፣አዋኪ ድርጊቶች እና ሌሎችም የደንብ መተላለፎች የመፈፀም እድላቸው ሰፊ እንደሆነ እና ያንን የመከላከለ ስራ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ