ጥር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት እንደምትወጣ ማስታወቋን ተከትሎ ውሳኔዋ የአለምን ብሎም የአፍሪካን የጤና ችግር ሊጎዳው እንደሚችል ስጋት እየተንጸባረቀ ነው፡፡
የአለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አባድር ዱላ ለጣቢያችን እንደተናገሩት የአሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት መውጣት ለአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡
በተለይም ለጤና ቢሮዎች በአቅም ግንባታ በኩልም ሆነ የተለያዩ ወረርሽኝ እና በሽታ ሲከሰት የሚደረገው ድጋፍ የሚታወቅ ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ላይ ከድጋፍ ተላቆ ራስን ለመቻል ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት፡፡
በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህረ አቶ አበራ ሄቢሶ በበኩላቸው አሜሪካ ከአለም ጤና ድርጅት አባልነት ለመዉጣት መወሰኗ የሚያሳድረዉን ተጽዕኖ በመረዳት፤ ኢትዮጵያም ሆነች የአፍሪካ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በማጠናከር ዉሳኔዉን የማስቀልበስ ተጽዕኖ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል በቀጣይ የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚደረገዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጉዳዩን በማንሳት መሞገት ይገባታልም ብለዋል፡፡
ድርጅቱ በክትባት መልክም ሆነ በተለያየ አማራጭ ለአፍሪካ አገራት ድጋፍ እንደሚያደርግ የሚታወቅ ሲሆን፤ ራስን ችሎ ለመስራት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ከሰሞኑን ባወጣው መግለጫው አሜሪካ ውሳኔዋን ዳግም እንድታጤነው መጠየቁ የሚታወቅ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ