በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት በተመዘገበው ”ሔር ኢሴ” በተሰኘው የኢሳ ማህበረሰብ ባሕላዊ መተዳደሪያ ሕግ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
”ሔር ኢሴ ለአብሮነትና ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለው ውይይት የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ በተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አሻ ያህያ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የጅቡቲና የሶማሊያ ተወካዮች፣ ዑጋዞችና የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡
በመድረኩ ከጂቡቲ ለሄዱት ልዑክም አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ በ”ሔር ኢሴ” ባሕላዊ ሕግ ላይ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ ፤”ሔር ኢሴ” የኢሳ ማህበረሰብን አስተሳስሮ ያኖረ ዘመን የተሻገረ ባሕላዊ ሕግ ነው ብለዋል፡፡
ሕጉ በኢትዮጵያ አቅራቢነት በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ አገራት በጋራ ቅርስነት በዓለም የማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ