በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ስርጭትን የሚያሳይ ጥናት እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እና በሁሉም ክልሎች ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ለመለየት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
እንደ ሀገር በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ላይ ባለሀብቶች እንዲሁም መንግስት የሚፈልገውን መረጃ ለማግኘት ከዚህ ቀደም በክልሎች የተጠናው ጥናት አጥጋቢ ባለመሆኑ ዳግም እንዲጠና መደረጉን ነው ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡
ጥናቱ ሲጠናቀቅ ከክልሎች ጋር በጋር እንደሚሰራበት የገለጹት ሚኒስትሩ ከዚህም ባሻገር የገጠር ኢንዱስትሪላይዜሽንን በ347 ወረዳዎች ለመጀመር ታቅዶ እስካሁን በ76 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ መደረጉን አመላክተዋል፡፡
በቀጣይ ይህ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ባለሀብቶችንም ተሳታፊ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉ ፋብሪካዎች በተለያዩ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል የሚል ጥያቄ የምክር ቤት አባል ያነሱ ሲሆን፤ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ማሻሻያው ከተደረገ ጀምሮ በዘርፉ የዋጋ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን አዎንታዊ ለውጦች መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ6 ወራት አፈጻጸሙ ለ127ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ