ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የቱሪዝም ሚኒስቴር የሆቴል ዘርፉን ለማጠናከር እና ለጉባኤው የሚመጡ ቱሪስቶችን ለመቀበል ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የገለጹት በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥ እና ደረጃ ምደባ ስራ አስፈጻሚ የሱፐር ዲቪዥን ዴስክ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አማረ ናቸዉ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንግዶቹን በልዩ ሁኔታ ለመቀበል ኢትዮጵያዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአለባበስ እና በመስተንገዶ ዝግጅት ከማድረግ ጀምሮ ሃገራዊ ገጽታን ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንግዶች የሚያርፉባቸውን 15 ሆቴሎች በተሰጣቸው የኮከብ ደረጃ መሰረት የሚሰጡትን አገልግሎት ጥራት በተመለከተ በተደረገው የድንገተኛ ፍተሻ ጥራቱን ባሟላ መልኩ አገልግሎት የማይሰጡ ሆቴሎችን የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉና 200 ሆቴሎችን ደግሞ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ድጋፍ እንደተደረገላቸው አመላክተዋል።
አሁን ላይ በሆቴሉ እና በቱሪዝም ዘርፍ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው የሚሉት ሃላፊው ከጉባኤው ባለፈ ክልሎችንም ለመጎብኘት ፍላጎት ለሚኖራቸው ቱሪስቶች የሆቴል አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ ደጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ