ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፋር ክልል እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መቀጠሉን ተከትሎ ከሰም ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት መመለስ እንዳይችል እንዳረገዉ እና ምርቱን ወደ አጎራባች ፋብሪካዎች የማዘዋወር ስራ እንደሚሰራ ያስታወቀው የአፋር ክልል ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው በክልሉ የገቢ ረሱ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ እንደሚሉት፤ በአፋር ክልል እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከትሎ ስድስት በሚጠጉ ቀበሌዎች ላይ ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል፡፡
በዚህም ምክንያት አሁንም ድረስ ተፈናቃዮች በካንፕ ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመው በተቻለ መጠን የዕለት ደራሽ ምግብ እና ለአርብቶ አደር ማህበረሰብ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን የማፈላለግ ስራም እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በተወሰነ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ባሳለፍነዉ ማክሰኞ በሬክተር ስኬል 4.7 የሚሆን የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡንም አስረድተዋል፡፡አክለውም በዞኑ የሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ ተግዳሮት በመሬት መንቀጥቅጡ እየደረሰበት መሆኑን ተከትሎ አሁንም ድረስ ጥገናውንም ሆነ ሰራተኛውን መመለስ አልተቻለም ሲሉ አብራርተዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ፋብሪካው ባለበት ቦታ በስፋት መታየቱን ተከትሎ ሰራተኛው ከስፍራው እንዲወጣ እና ነዋሪዎች በቦታው እንዳይገኙ ጥበቃዎችን እየተደረጉ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡ፋብሪካው 20ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን ተከትሎ ምርቱን መቀጠል እንዲችል አጎራባች የሆኑ ፋብሪካዎች የመጠቀም ስራ ይሰራል ብለው፤ፋብሪካው እየገጠሙት ባሉ ችግሮች ሳቢያ በፋብሪካዉም በሰራተኞቹም ላይ ከፍተኛ ችግር መደቀኑን ገልጸዋል፡፡
በአፋር ክልል በተደጋጋሚ በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ