በመዲናዋ በህንጻ ተደራሽነት ዙሪያ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ አካል ጉዳተኞች ለመንግስት አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ ከተቋቋመባቸው አላማዎች አንዱ የሕብረተሰቡን አቤቱታ እና ቅሬታ ተቀብሎ የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሠጥ ማድረግ ነው የሚሉት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ፣ አካል ጉዳተኞችም የመብት ጥሰት ሲፈጸምባቸው የአካል ጉዳት ከሌለባቸው ዜጎች ጋር እኩል ፍትህ እንዲያገኙ እና መብታቸው እንዲጠበቅ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከአካል ጉዳተኞች ከሚመጡ አቤቱታዎች ባሻገር ኮሚሽኑ በራሱ ምርመራ በማድረግ ቅሬታቸውን በግልጽ እንዲያቀርቡ እና መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
በዚህ ሂደትም በቅርቡ ኮሚሽኑ በአዲስ አባባ ከተማ ከህንጻ ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ አዘጋጅቶ 15 አካል ጉዳተኞች ቅሬቻውን ለመንግስት አካላት ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም አካል ጉዳተኞች ላቀረቧቸው አቤቱታዎች ምላሽ መስጠታቸውን ኮሚሽነሯ አክለዋል፡፡
መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ እንደ መብት ተቀብሎ፣ የሚጠበቅበትን እንዲሰራ ግፊት እንደሚያደርጉ እና የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦች ስለመፈጸም አለመፈጸማቸው ክትትል እንደሚያርጉም ነው የተናገሩት፡፡
በየተቋማቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የስራ አካባቢ እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ለማድረግ እና መብታቸው እንዲከበር ኮሚሽኑ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ