ታኅሳስ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የገና በዓልን ተከትሎ 6 ቀለል ያሉ አደጋዎች መከሰታቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ከስድስቱ አደጋዎች አራቱ የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ በግባቡ ባልጠፋ ከሰል ምክንያት በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተከሰተ ቀላል አደጋ ነው ሲሉ አቶ ንጋቱ ገልጸዋል። በከሰል መታፈን ምክንያት በስምንት ሰዎች ላይ ለሞት ያላደረሰ አደጋ ተከስቷል ሲሉም ህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ገልጸዋል።
የእሳት አደጋውም በመኖሪያ ቤት ላይና በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ የተከሰተ ነው ብለዋል። በሁለቱም አደጋዎች የሰው ህይወት ባያልፍም ህብረተሰቡ በበአል አከባበሩ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ግን የተከሰቱት አደጋዎች አስረጂ ናቸው ሲሉ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።
በየጊዜው በበአል ወቅት ከሚሰማውና ከሚደርሰው አደጋ አንጻር ያሁኑ ቀላል የሚባል ቢሆንም የበአሉ ድባብና እንቅስቃሴ አሁንም ያላለቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉን እንዲቀጥል ሲሉ አቶ ንጋቱ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube
ምላሽ ይስጡ