ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያየ ጊዜ በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የአንበሶች ቁጥር መቀነስ በዋነኝነት የመኖሪያ ቦታቸው መጥፋት እንደሆነ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን #ለመናኸሪያ #ሬዲዮ ገልጿል፡፡
በባለስልጣኑ የዘርፉ ተመራማሪና ዶ/ር ጽዮን አስፋው እንደሚገልጹት በሃገሪቱ አሁን ላይ አንበሶች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ እንዲሁም አንበሳ ከማህበረሰቡ ጋር ያለዉን መስተጋብርና ቁርኝት በኦሞ ስምጥ ሸለቆ በላይኛዉም በታችኛዉም፣ በተለያዩ ፓርኮች እና ጥብቅ ደኖች ላይ ጥናት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ጽዮን እንደሚገልጹት የአንበሳ ቆዳን እና ጭራን ለባህል መድኃኒትነት የመጠቀም ነገር በተለይም እንስሳቶቹን ለህገወጥ አደን ይበልጥ ተጋላጭ እንዲሆኑና ቁጥራቸው እንዲመናመን ሆኗል ብለው በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ባህል አንበሳ መግደል እንደ ጀግንነት የመቁጠር እሳቤ በመኖሩ፣ ከብቶቻችንን ይበሉብናል ብለው ስለሚፈሩ እንደሚገሏቸዉም ዶ/ር ጽዮን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል አንበሳ በፍጥረት ባህሪው ሰፊ የመኖሪያ ስፍራ የሚፈልግ እንስሳ በመሆኑ ጥብቅ ደኖች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ የሚኖሩ የኢንቨስትመንት ስራዎች፣ አንበሶቹ ለምግብነት የሚፈልጓቸው እንስሳት ቁጥር መመናመን በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር በማድረጉ፣ የህገ ወጥ ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና ግጦሽ መበራከት የአንበሶች ቁጥር ለመቀነሱ በከፍተኛ ሁኔታ አስተዋጽዖ አድርጓል ብለዋል፡፡
ተመራማሪዋ አክለዉም በሃገራችን ዱር እንስሳት አጠባበቅ ዙሪያ የተለያዩ አዋጅ እና የህግ ማዕቀፍ ቢኖርም ተፈጻሚነቱና የተሰጠው ትኩረት አናሳ እንደሆነ ገልጸው መንግስት ትኩረት እንዲያደርግ ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ በተደረጉት ጥናቶቸ አሁን ላይ የአንበሶች ቁጥር ከ9መቶ እስከ 1ሺህ እንደሆነ ይገመታል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ