ጥር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኦቪድ ሪል እስቴት አራት ኪሎ ጥይት ቤት ተብሎ በሚታወቀው አከባቢ ኪንግስ ታወር በሚል እየገነባ ከሚገኙ መኖረያ ቤቶች መካከል ግንባታቸው የተጠናቀቁ 249 መኖሪያ ቤቶችን የያዙ ሶስት ብሎክች በትናንትናው እለት ለባለቤቶቹ አስተላለፏል፡፡
ኦቪድ ሪል እስቴት ተገጣጣሚ የሆኑ ቤቶችን በአራት ወራት ውስጥ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ በማስተላለፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ በሁለተኛው ምዕራፍም ቀሪ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ለማስተላለፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በኦቪድ ሪል እስቴት የሳይት ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ኖላዊ ተፈራ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ረል እስቴቱ ሁሉም ሰው በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ቤት እንዲያገኝ በማሰብ በልዩ ትኩረትና አማራጮች የቤት ጭያጮችን በማከናወን ላይ ይገኛል ያሉት ኃላፊው፤በሁለተኛው ምዕራፍ 1 ሺህ ያህል አባወራዎችን የሚይዙ አስራ ሰባት ብሎኮችን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አመላክተዋል፡፡
ቤቶቹ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ምን ያህል ትኩረት አድርጋችሁ ትሰራላችሁ ያልናቸው ኃላፊው፤ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሳምንቱን በሙሉ ለ24 ሰዓታት በመስራት የቆይታ ጊዜያቸው እንዲያጥር ብሎም የአቅርቦት ችግር እንዳይኖር ድርጅቱ እህት ድርጅቶችን በማቋቋም የአቅርቦትና የጥራት ችግር እንዳይኖር ለማስቻል በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ኦቪድ ሪል እስቴት አሁን ላይ በአራት ወራት የሚደረሱ ተገጣጣሚ ቤቶችን በመስራት ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ምላሽ ይስጡ