ኤል ቹሎ እና የቡድኑ የአማካኝ መስመር ተጫዋች የሆነው ፓብሎ ባሪዮስ በቅድመ ጨዋታ መግለጫ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
ታዲያ ዲዬጎ ሲሚዮኒ በዚ ክለብ ይህ ታሪክ እውን ሆኖ አያውቅም። ግን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መከራ ማሳካት የሁሉም ክለብ ራዕይ ነው።
እኛ ዘንድሮ ቢያንስ ለፍፃሜው መድረስ እንፈልጋለን ሲል ተደምጧል። ኤል ቹሎ በስፔን ላሊጋ ብዉ አመት አንድ ክለብ ማሰልጠን የቻለ ግለሰብ ነው።
ከ10 አመት በላይ አትሌቲኮ ማድሪድን አሰልጥኗል። በቆይታው 2 የስፔን ላሊጋ ፤ 1 የኮፓ ዴል ሬ ፤ 2 የዩሮፓ ሊግ ፤ እና 2 ሱፐር ካፕ ማሳካት ችሏል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ለማሳካት 2 ጊዜ ለፍፃሜው ቢደርስም 2ቱንም በከተማ ተቀናቃኛቸው ሪያል ማድሪድ በመሸነፍ ዋንጫውን ማሳካት አለመቻላቸው አይዘነጋም።
አትሌቲኮ ማድሪድ በስታዲዮ ሪያድ air ሜትሮፖሊታኖ ከሌላው ጠንካራ ቡድን ባየር ሌቨርኩዝን ጋር ዛሬ #ምሽት 5:00 ሲል የሚገናኙ ይሆናል።
በሚካኤል ደጀኔ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ