ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ከመጡት ውስጥ 25ሺህ 581ዱ ብቻ በመዲናዋ የሚጠየቀውን መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው ባለፉት 6 ወራት በጥቅሉ 57ሺህ 214 ያህል የነዋሪነት መሸኛ መረጃዎችን ሲያጠናቅር እንደቆየና በመጨረሻም በትክክል መስፈርቱን አሟልተው የተገኙት 25ሺህ 581 ያህሉ ብቻ መሆናቸውን የሲቭል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ አስታውቀዋል።
ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት መሸኛ አስገብተው ማስረጃቸው ተቀባይነት ያገኙት የፋይዳ ምዝገባ እንዲያካሂዱ መስፈርቱ እንደሚያስገድዳቸው አቶ ዮናስ አስታውቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ 9ሺህ 504 ያህል ዜጎች ቀርበው ሪፖርት በማድረግ ባለፉት 6 ወራት አገልግሎቱን ማግኘታቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ግለሰቦች ከተለያየ ቦታ ይዘውት የሚመጡት መሸኛ የከተማውን ሰላምና ደህንነት እንዳያውክ ሲባል ብቻ ዘርፈ ብዙ ምርመራ እንደሚደረግበት የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በከተማ ደረጃ መሸኛቸው ከተጣራ በኋላ በድጋሜ ከመጡበት ወረዳም የማመሳከር ስራ ስለሚሰራ ምላሽ ለመስጠት መዘግየት ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ